ወደ አዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ድርጅት እንኳን ደህና መጡ፤ የገበያ መረጋጋት እና የአቅርቦት ዋስትና አጋርዎ

ከዘመናዊ የንግድ አሰራር እስከ ጥራት ያለው የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር፤ የከተማዋን ነዋሪዎች ፍላጎት መሰረት ያደረጉ እና ለላቀ ውጤት የተለሙ አገልግሎቶችን እናቀርባለን።

የእኛ ታሪክ

የንግድ እና አቅርቦት አገልግሎት ሙያዊ ብቃት ታማኝነት/ጥንቃቄ

የአዲስ አበባ የንግድ ሥራዎች ድርጅት በመነሻ ካፒታል ብር 7.25 ቢሊየን ሐምሌ 15/2015 ዓ/ም በደንብ ቁጥር 152 ተመሰረት፡፡ ድርጅቱ ለከተማ አስተዳደር ሸማቹ ህብረተሰብ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የንግድ እቃዎችን በቀጥታ ከአምራቹ ጋራ የገበያ ትስስር በመፍጠር በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ አገልግሎት እንዲሰጥ የተቋቋመ ድርጅት ነ፡፡ በመጀመሪያ 1 አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ብር 85,226,825.22 ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ድርጅቱ ከከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ድጋፍ ቢሮና መጋዘን ያለው ሲሆን ለድጋፍና ክትትልም ምቹ ስፍራ ላይ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ በደንብ ቁጥር 152/2015 ዓ.ም ቢቋቋምም ወደ ስራ የገባው ሚያዝያ 2016 ዓ.ም ነው፡፡ ድርጀቱ የመጀመሪያ ስራ አሰኪያጅ በሆኑት በአቶ መስፍን አሰፋ እየተመራ የገኛል፡፡  

photo 2026 03 09 14 16 18

2

አመታት የአገልግሎት ዘመን

500K

በመላው አዲስ አበባ ያሉ ደንበኞቻችን

642

በአዲስ አበባ የተከናወኑ ተግባራት

የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደታችን

መሰረታዊ አገልግሎቶቻችንን የሚያገኙባቸው ቅደም ተከተሎች

1. ምዝገባ እና ጥያቄ

ተጠቃሚዎች የሚያስፈልጓቸውን መሰረታዊ ሸቀጦች ወይም ተቋማዊ አገልግሎቶች በመለየት በአካል በቅርንጫፎቻችን በመገኘት ወይም በድረ-ገጻችን አማካኝነት ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ። በዚህ ደረጃ አስፈላጊው መረጃ ተሰብስቦ ለቀጣይ ዝግጅት ዝግጁ ይደረጋል።

2. ማረጋገጥ እና ዝግጅት

የቀረቡ ጥያቄዎች በድርጅታችን ባለሙያዎች አማካኝነት ፈጣን ምላሽ ያገኛሉ። የአሰራር ሂደታችን ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን የተከተለ ሲሆን፣ ምርቶች በጥራት እና በብዛት ተለይተው ለስርጭት እንዲዘጋጁ ይደረጋል።

3. ስርጭት እና አቅርቦት

በመጨረሻም ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለነዋሪዎች፣ ለሸማች ማህበራት ወይም ለተቋማት ይሰራጫሉ። ምርቶቹ በሁሉም የከተማዋ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ማእከላቶቻችን አማካኝነት ለህዝብ ተደራሽ ይሆናሉ።

photo 2026 03 08 20 09 43 (2)

ዋናው ግባችን

ተልዕኮአችን

የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሃገራት ገዝቶ በማቅረብ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በማምረት፣ በማስመረት፣ ክምችት በመያዝ እና በከተማዋ ለሚገኙ የመሰረታዊ ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት፣ ለአገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና ለሸማቹ ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማሰራጨት ገበያ ማረጋጋት ነው፡፡

ወደፊት የሚታዩ እቅዶች

ራዕያችን

በ2022 ዓ.ም በሀገሪቱ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም ሰፊ የገበያ ድርሻ ካላቸው ትርፋማ የልማት ድርጅቶች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ ማየት፤

የስራ ቡድናችን

የስራ አመራር አባላቶቻችንን ይወቁ

aa6
አቶ መስፍን

ዋና  ስራ አስኪያጅ

aa8
አቶ ጥላሁን

የብርሃን ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ

aa10
አቶ አበበ

የጉለሌ እንጀራ ፋብሪካ ስራ አሰኪያጅ

gemini generated image j7khf7j7khf7j7kh min

ለማህበረሰባችን መመለስ

የማህበረሰብ ተሳትፎ

ድርጅታችን በተለያዩ ተግባራት ማህበረሰቡን መደገፍ እና ለወገኑ የሚተርፍ ስራ መስራት ትልቅ እሴቱ እንደሆነ ያምናል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ የአቅርቦት ድጋፎችን በማመቻቸትም ሆነ የተለያዩ ማህበራዊ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ፣ በከተማችን ነዋሪዎች ህይወት ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር በቁርጠኝነት እንሰራለን።

አስተማማኝ እና ተመጣጣኝ የገበያ አቅርቦት ለማግኘት ዝግጁ ነዎት ?

ስለ ምርቶቻችን እና አገልግሎቶቻችን ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ዛሬውኑ ያግኙን።

Scroll to Top